ሀ. መታዘዝ ከመስዋዕት ይበልጣል
' እነሆ መታዘዝ ከመስዋዕት፣ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል።'
ሳኦል በትክክለኛ ጊዜ አልታዘዘም
“ ሳኦልም፦ ህዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደተበታተኑ፣ አንተም በቀጠሮው እንዳልመጣህ፣ ፍልስጤማውያንም ወደ ማክማስ እንደተሰበሰቡ አየሁ። . . . ስለዚህ ሳልታገስ የሚቃጠል መስዋዕትን አሳረግሁ፡ አለ። “
1ኛ ሳሙ 11-12
“ ሳኦልም፦ ዳዊትን ከግ ንቡ ጋር አጣብቄ እመታዋለው ብሎ ጦሩን ወረወረ። “
1ኛ ሳሙ 18:12
ከምናቀርብለት ምስጋናና ዝማሬ ይልቅ እግዚአብሔር እንድንታዘዘው ይፈልጋል። መታዘዝ የጎደለው አግልግሎትም ሆነ መስዋዕት ተቀባይነትን ከማጣቱም በላይ ተራፊምን እንደማምለክና ምዋርተኛ የመሆንን ያህል ይቆጠራል። ከመታዘዝ የሚጀምር መስዋዕት ግን ለበረከትና ለድል ህይወት የሚያጋልጥ ነው።
“ እሺ ብትሉ ለእኔ ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላቹ ። “
ኢሳ 1፡18
“በእርሱም ስለ ስሙ በአህዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሳ መታዘዝ እንዲገኝ ፀጋንና ሐዋሪያነትን ተቀበልን። “
ሮሜ 1፡5
“ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ። “
ዮሐ 14፡15
“ እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል።”
ዮሐ 9፡31
2. የተሰበረ ልብ ከመስዋዕት ይበልጣል
መስዋዕትን ብትወድስ በሰጠሁህ ነበር፣ የሚቃጠለውንም መስዋዕት ደስ አያሰኝህም። የእግዚአብሔር መስዋዕት ደስ አያሰኝህም። የእግዚአብሄር መስዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።”
መዝ (51)16 - 17
3. ምህረት ማድረግ ከመስዋዕት ይበልጣል
“ ምህረትን እወዳለው መስዋዕትን አይደለም። “
ማቴ 12፡7
“ እንግዲህ መባህን በመሰዊያው ካይ ብታቀርብ፣ በዚያም ወንድምህ እንዳች በአንት ላይ እንዳለው ብታስብ፣ በዚያ በመሰዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፣ አስቀድመህም ከወምድምህ ጋር ታረቅ በኃላም መባህን አቅርብ።”
ማቴ 5፡23- 24
4. እግዚአብሔርን ማወቅ ከመስዋዕት ይበልጣል
“ ከመስዋዕት ይልቅ ምህረትን፣ ከሚቃጠል መስዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እወዳለሁና።”
ሆሴዕ 6፡6
- ከመረጃ የሚገኝ እውቀት፦ በትምህርት፣ ከተለያዩ ሚዲያዎች በመስማትና ሁኔታዎችን በማየት መረጃዊ የሆነ እውቀትን ማግኘት እንችላለን። ሆኖም ግ ን እውቀት በቀጥታ ከአእምሮአችን ጋር ብቻ ይገኛል።
- ከመተዋወቅ የሚገኝ እውቀት፦ ይህ እውቀት ከመገናኘት ውስጥ የሚፈጠር ሲሆን በአብዛኛው በመካከል ሆኖ የሚያስተዋውቅን አካል ይፈልጋል ይህም በመካከል ያለ አስተዋዋቂ የሚተዋወቁትን አካሎች በየተናጠል ያወቀ መሆን ይኖርበታል። ለመገናኘት ቦታና ጊዜ ወሳኞች ናቸው። ለምሳሌ ሰዎች ጌታን እንድግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉበትን ቀንና ቦታ ሁልጊዜም የሚያስታውሱት፣ በየአመቱም መታሰቢያ የሚያደርጉለት ለመጀመሪያ ጊዜ የመተዋወቂያቸው ክስተት ነው።
- ህብረት ከማድረግ የሚገኝ እውቀት፦ ይህ እውቀት አብሮ መዋልን፣ ማደርን፣ አብሮ ማሳለፍል፣ መውጣትን መግባትን ይጠይቃል። የመተዋወቁም ጥልቀት ከሌሎች የላቀና የደረጀ ነው። በተለይም ደግሞ በባህሪ፣ በንግግርና በአስተሳሰብ ሁሉ ላይ ተፅዕኖ የሚያመጣና መመሳሰልን የሚፈጥር ከፍተኛው የእውቀት ድረጃ ነው።
“ እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላቹ ፣ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን።”
ዮሐ 4፡22
“ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን፣ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ህይወት ናት።”
ዮሐ 17፡3
5. ፅድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ ከመስዋዕት ይበልጣል
“ እግዞአብሔር ከመስዋዕት ይልቅ ፅድቅንና ቅን ነገርን ማድረግ ይወድዳል።”
ምሳሌ 21፡3
“መልካም ብታደርግ ተቀባይነትን አታገኝምን?”
ዘፍ 4፡6 (አ.መ.ት)
6. መውደድ ከመስዋዕት ይበልጣል
“ በፍፁም ልብ በፍፁም አእምሮም በፍፁም ነፍስም በፍፁም ሃይልም እግዚአብሔርን መውደድ ባልንጀራንም እንደራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መስዋዕትና ከሌላው መስዋዕት የሚበልጥ ነው።”
ማር 12፡33
Related Posts
ከመስዋት የሚበልጥ (በኑሮ የሚገለጥ አምልኮ)
…በኑሮ የሚገለጥ አምልኮ በህልውናው ውስጥ ለሚደረግ የግንኙነት አምልኮ መሠረት ነው። የግ ንኙነት አምልኮ በኑሮ ለሚገለጠው አምልኮ ጉልበት የሚሰጥ ነው…